free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

የሸይጧን ወጥመዶች


✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

=<({አል-ቁርአን 35:6})>=


{6} በእርግጥ ሸይጧን ላናንተ ጠላት ነው። እናም ጠላት አድርጋችሁ ያዙት። ተከታዮቹን የሚጣራው ከዕሳት ጏደች እንዲሆኑ ብቻ ነው።

የኢብሊስ(የሸይጧን) ታሪክይሰግዱ በጨረፍታ

ሸይጧን ጭስ አልባ ከሆነ እሳት የተፈጠረ ሲሆን መላኢካ ባይሆንም ለአሏህ በነበረው ታዛዥነት ግን በጀነት ከነሱ መካከል ነበር። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) አደም(ዐ.ሰ) በፈጠረ ጊዜ በጀነት ያሉ ሁሉ ከአደም(ዐ.ሰ) ፊት ለፊት ዘንድ አዘዛቸው። ነገር ግን ሸይጧን በእብሪተኝነት እና በኩራት እንዲህ በማለት አሻፈረኝ አለ

=<({አል-ቁርአን 7:12})>=

አሏህም
{12} እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ። እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው አለ።

አሏህም ሸይጧንን ረግሞት ከጀነት አባረረው። ሆኖም ግን ሰዎችን የሚያጠምበትን እድል ይሰጠው ዘንድ ጠየቀ፤ የጠየቀውን ነገር ሰጠው።

=<({አል-ቁርአን 7:16-17})>=

ሆነው
style{16} ስለአጠመምከኝ ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ አለ።

{17} ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ፣ ከኋላቸው ፣ ከቀኛቸውና ከግራቸው በኩል በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ። አብዛሃኛዎቹንም አመስጋኝ አታገኛቸውም አለ።

የሸይጧን ወጥመዶች


እንደሚታወቀው የእስልምና ሃይማኖት መሠረቱ ተውሂድ ወይም አሃዳዊነት ነው። ይህም አሏህ የዚህ ዩኒቨርስ ፈጣሪና styleአስተናባሪ ፣ ሰጭ ፣ ነሽ መሆኑን እንዲሁም የአምልኮት ተግባራት በሙሉ ለአሏህ ብቻ ማድረግንና ልዩና ውብ የሆኑ ስሞችና ባህሪያቶች እንዳሉት ማረጋገጥ እና ማመን ነው። ከዚህ በተቃራኒ ከአሏህ ዘንድ ከበደሎች ሁሉ የከፋ በደል ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል ብሎ ማለት በአሏህ ላይ ማጋራት ነው። ለምሳሌ፦

* የአምልኮት ተግባራትን ከአሏህ ውጭ ላሉ ነገራት ማድረግ(ከአሏህ ውጭ የሆኑ ነገሮችን መለመን ፣ ለነሱ ማረድ ፣ መስገድ ፣ በነሱ መመካት ወ.ዘ.ተ)

* የአሏህን ስምና ባህርያት አለመቀበል ወይም በፍጡራኖቹ መመሰል ትርጉማቸውን መቀየር ወ.ዘ.ተ

* አሏህ ልጅና እናት አለው ወይም ደግሞ ሌላ ባላንጣ አለው ብሎ ማመን

የሸይጧን ዋና ግቡ የሰው ልጆችን ማጥመም ሲሆን ነገርግን ሸይጧን ግልፅ የሆነ ክህደቶችን እንዲፈፅሙ ማድረግ ካልቻለ ሌላ አማራጮችን ይጠቀማል። ለምሳሌ የሩቅን አዋቂ አሸናፊ ጥበበኛ አሏህ ብቻ ሆኖያለ ሰዎች በጥንቆላ ፣ በድግምት ፣ በኮኮብ ቆጠራ ወ.ዘ.ተ እንዲያምኑ ለማድረግ ይሞክራል።

ሌላኛው የሸይጧን ሴራ ሰዎች የተሳሳተ አቂዳ በኢስላም እንዲይዙ ማድረግ ሲሆን ይህም አሏህ(ሱ.ወ.ተ) እና መልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ያልደነገጉትን ነገር መስራት ነው። በሌላ አገላለፅ የዕምነቱን ክፍል የሚጣረሱ ነገሮችን ከራስ ፍላፍልስፍናና ስሜት በመነሳት ያልነበሩ ነገሮች የዕምነቱ ክፍልና የአዕምኮት ተግባራት አድርጐ መያዝን ያስከትላል።

በእርግጥ እነዚህ የቢድአ ሰዎች ኢስላም በራሱ ሙሉ እንዳልሆነ በማመን ወይም መለኮታዊ ራዕይ በትክክል እንዳልተገለፀ በማመን ወደ ቢድአ ነገራቶች ይዘምታሉ። ይህ ግን ግልፅ የሆነ ክህደት ነው። ምክኒያቱም አሏህ የገለፀውን ነገር መካድ ነውና። አሏህ በቁርአኑ በሱረቱ አል-ማኢዳ አንቀፅ 3 ላይ እንዲህ ይላል

=<({አል-ቁርአን 5:3})>=-


{3} ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋየንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ለናንተም ከሃይማኖት በኩል ኢስላምን መረጥኩ።

አሏሁ አዘወጀል በቁርአኑ በሱረቱል ማኢዳ አንቀፅ 91 ላይ እንዲህ ይላል

=<({አል-ቁርአን 5:91})>=


{91} ሸይጧንም የሚፈልገው አሏህን ከማውሳትና ሊያግዳችሁ ብቻ ነው።

አሏህ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ የተወሰኑ ስራዎችን ግዴታ ያደረገ ሲሆን ከሶላትለጊዜው አምስት አውቃ ሶላቶችን መጥቀስ በቂ ነው። ሸይጧንም ብዙ ሃጢያቶችን እንድንሰራ በመሻት ሶላቶቻችነን ችላ እንድንልና ብሎም ከሶላት እንድንርቅ ለማድረግ ይሞክራል።

=<({አል-ቁርአን 29:45})>=


{45} እነሆ ሶላት ከመጥፎና ከተጠላ ነገር ከልካይ ናት።

እንዴት የጣዖት አምልኮት እንደተጀመረ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የገለፁልን ሲሆን ይህም በሸይጧን ትዕግስትና የቀስበቀስ የማጭበርበር ዘዴ ነበር። በነብዩሏህ ኑህ(ዐ.ሰ) ዘመን የነበሩ ሷሊህ ሰዎች ከሞቱ ብኋላ ሸይጧን መጣና ደግነታቸውን ለማስታወስና ለክብራቸው ሃውልት styleበዙርያችሁ ይቁምላቸው ሲል ገፋፋቸው። ያ ትውልድ ባለፈ ጊዜ ሰዎች ሃውልቶቹ ለምን እንደቆሙ ረሱ። ሸይጧንም የአባቶቻችሁ አባቶች ያመልኴቸው ነበር፤ በነርሱም ምክኒያት ዝናብ ይጥል የነበረው ሲል አጭበረበራቸው። ሰዎቹም እነዛን ሃውልቶች ማምለክ ጀመሩ።

ይህ ቀስበቀስ የማጭበርበር ዘዴ በብዙ መንገድ ይጠቀምበታል። ለምሳሌ ሰዎች ዝሙት ይፈፅሙ ዘንድ አጅነብይ የሆነችን ሴት(ወንድ) እንድንመለከት በማድረግ ይጀምርና ስለሷ እንድናስብ ብሎም ፈገግ እያልን እንድንስቅ እንድንጫወት ይጋብዘናል። በመጨረሻም ብቻችነን ተገናኝተን እንድናወራ በመጋበዝ የከፋ ሃጢያት ላይ ይጥለናል።

በተመሳሳይ መልኩ ሱና ሶላቶቻችነን እንድንተው በተለያዩ በማይረቡ ምክኒያቶች ያሳምነንና ከዛም ግዴታ የሆኑትን ሶላቶች እንዳንሰግድ ያዳክመናል። ይህን ተከትሎም ግዴታ ሶላቶቻችነን እስከመተው ወይም ችላ እሰከማለት እንደርሳለን።

ሸይጧን ሃጢያት ነገሮችን አስውቦ ለሰዎች ያቀርባል። አደምና ሐዋን በዛች ከበደለኞች በምታደርጋቸው ዛፍ እንዴት እንዳታለላቸው ማስታወስ በቂ ነው። ሸይጧን ለአደም(ዐ.ሰ) እንዲህ ሲል ሹክ አለው


=<({አል-ቁርአን 20:120})>=


{120} አደም ሆይ! ህያው(ዘላለማዊ) ወደ ምታደርግህ ዛፍና ዘላለማዊ ወደሆነው ግዛት አላመላክትህምን? አለው።

ብዙ ሐላል የነበሩ ምግቦች በአደም(ዐ.ሰ) ዙርያ ቢኖርም ሸይጧን ግን ከዛች ሐራም ከሆነች ዛፍ እንዲመገብ ገፋፋው።

=<({አል-ቁርአን 6:43})>=

{43} ይጠሉት የነበሩትንም ነገር ሸይጧን አሳመረላቸው።

ሸይጧንን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን

በመጀመሪያ ደረጃ ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር ሸይጧን የኛ ግልፅ ጠላት መሆኑን መገንዘብና ጠላት አድርገን መያዝ ነው። የጠላታችነን ማንነት ካወቅን ያኔ እሱን ማሸነፍ እንችላለን። የሸይጧን ሃይል ወይም አቅም ያለው የማታለል ብቃቱ ላይ ነው። ሆኖም እራሳችነን ከሸይጧን ተንኮል ለመጠበቅ የሚወስዳቸውን እርምጃዎችና ስልቶች እንዲሁም የተለያዩ ዘዴዎቹን መረዳት ይኖርብናል።

የአሏህን ጥበቃና ከለላ መለመን እንዲሁም በሱ ላይ መመካት ሸይጧንን ማሸነፊያ አይነተኛ መሳሪያ ነው። ሱረቱል አል- ፈለቅና ሱረቱ ናስ አዘውትረን በመቅራት ከሸይጧን ተንኮል በአሏህ መጠበቅ እንችላለን። ሆኖም ግን በህይወት እስካለን ድረስ ሸይጧን መቼም ቢሆን እጅ አይሰጥም፤ እኛን ለማጥመም ደከመኝ ሰለቸኝ አይልም። ስለዚህ ዘወትር አሏህ ይመራንና ይጠብቀን ዘንድ እሱን መለመን ይኖርብናል።

በሸይጧን ሴራ ከተሸነፍን በአሏህ እዝነትና ቸርነት ህይወታችነን የምናስተካክልበት ሌላ እድል አለን።
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ሸይጧን ለሃያሉ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) እንዲህ አለ "አምላክ ሆይ በልቅናህ ይሁንብኝ ባሮችህን ለማጥመም መሞከሬን እቀጥላለሁ ነፍሳቸው በአካላቸው እስካለች ድረስ" አለ። ጌታ(አሏህ) "በልቅናየ ይሁንብኝ ምህረቴን እሰከለመኑኝ ድረስ እነሱን መማር እቀጥላለሁ አለ" ብለዋል።

{አህመድ}

ተውበት ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ቅንና እውነተኛ እንዲሁም ከልብ የመነጨ መሆን ይኖርበታል። እንዲሁም ያን ወንጀል ወይም ሃጢያት ደግሞ ላለመፈፀም ማሰብንና ቆራጥ ውሳኔን መወሰን ይጠይቃል።

አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ከዛች ዛፍ በከለከለው ጊዜ ከዚህ ዛፍ አትብላ አይደለም ያለው። ይልቁንም በሱረቱል በቀራ አንቀፅ 32 ላይ እንደገለፀው "ወደዚህ ዛፍ አትቅረቡ" ሲል ነበር የከለከለው። ስለዚህ ወንጀል እንድንፈፅም ከመሚመሩን ነገሮች በሙሉ እራሳችንን ማራቅ ይኖርብናል ማለት ነው።



እኛ ወጣቶች እንደመሆናችን መጠን ብዙ ጊዜ በጏደኞቻችን ተፅዕኖ ስር እንወድቃለን። ሆኖም ጏደኞቻችን መጥፎ ከሆኑ የኛም ማንነት የጏደኛችነን ማንነት ነው ሊመስል የሚችለው። ስለዚህ መጥፎ ጏደኛ አሏህን ወደ ማመፅ እንጅ ወደ ኸይር ነገር ስለማይመራ የኛ ምርጫ አሏህን የሚታዘዝ ፣ የከለከለውን ነገር የሚከለከል ፣ መልካም ነገር እንድንሰራ የሚያበረታታን መሆን ይኖርበታል።

=<({አል-ቁርአን 7:200})>=


{200} ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያገኝህ በአሏህ ተጠበቅ። እርሱ ሰሚም አዋቂም ነውና።

በመልካም ስራዎች ግዜያችነን ካሳለፍን ለመጥፎ ስራዎች ቦታ አይኖረንም። እንዲሁም በሸይጧን ሴራ በቀላሉ ከመሸነፍ እንድናለን።

አሏህ ሃጢያቶቻችነን ይምረን ዘንድና ከሸይጧን ወጥመዶች ይጠብቀን ዘንድ ውብ በሆኑ ስምና ባህሪያቶቹ እለምነዋለሁ።

Iqra
Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
Iqra
1426

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


Old school Easter eggs.